elias

Sun, 18 Jan, 2026 at 11:00 am UTC+03:00

Idoro, | Addis Ababa

\u1218\u1295\u1348\u1223\u12ca  \u121d\u1230\u120e\u1278
Publisher/Hostመንፈሣዊ ምሰሎቸ
elias
Advertisement
መጋቢት 27/2017 #መድኃኔዓለም (ጥንተ ስቅለት)
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን መጋቢት 27 ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አለምን ለማዳን ለኛ ለልጆቹ ዋጋ ሊከፍል #በእፀ_መስቀል የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱን የምናስብበት አመታዊ ክብረ በአል ነው
የማይሞት እርሱ ሞተ ሙታንን ያድናቸዉ ዘንድ ሞተ
ሞትን ይሽረዉ ዘንድ ሞተ
✝️️ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን ሮሜ.6፥5
✝️የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ዓለም ድህነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው
✝️ሐዋርያው #ቅዱስ_ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ቆሮ.1፥1-18 እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው
✝️ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው ማቴ.27፥35-75 ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው
✝️በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው #በስቅለቱና_በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት #መልካሙ_ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ

✝️ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ ማቴዎስ.27፥45 ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት #ሐዋርያዉ_ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች
✝️ጌታ #ሁሉ_ተፈፀመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው በሰማይ ማቴ.24፥29፤27፥45
👉ፀሐይ ጨለመች
👉 ጨረቃ ደም ሆነች
👉 ከዋክብት ረገፉ
👉የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ
👉ምድር ተናወጠች
👉መቃብሮች ተከፈቱ
👉አለቶች ተፈረካከሱ
👉በእርሱ ቁስል #እኛ_ተፈወስን ኢሳ.53-5 እርሱ የሾህ አክሊል ተደፍቶበት ለእኛ የክብር አክሊል ደፋልን ጐኑን በጦር ተወግቶና ቆስሎ ለዘለአለም ፈወሰን ተጠማሁ እያለ እኛን የሕይወት መጠጥ አጠጣን
👉አንዱ #ስለ_ሁላችን_ሞተ የእኛን ቅጣት ወሰደ ሞታችንን ሞተ ገነትን እንድንወርስና በሕይወት እንኖር ዘንድ ሞተ መርገማችንን ወሰደ
👉ስለዚህ እኛም የጌታችን የመድሃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ስቅላት ሞት ስናስብ #የኢየሱስ_ክርስቶስ መሞት የሰው ልጆች የጥል ግድግዳ ፈርሶ ፍቅር የተመሰረተበት ዕለት ነውና ምንም ቃላት ባይገኝለትም ክብር ምስጋና ዋጋ ከፍሎ ላዳነን በምህረት አይኑ ለጎበኘን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
Advertisement

Event Venue & Nearby Stays

Idoro,, Addis Ababa, Ethiopia

Icon
Concerts, fests, parties, meetups - all the happenings, one place.

Ask AI if this event suits you:

More Events in Addis Ababa

\u1213\u134a\u12db \u1200\u1260\u123b
Thu, 22 Jan at 12:30 am ሓፊዛ ሀበሻ

Addis Ababa, Ethiopia

Ethiopia Food & Kitchen
Fri, 23 Jan at 10:00 am Ethiopia Food & Kitchen

Millennium Hall

Addis Ababa is Happening!

Never miss your favorite happenings again!

Explore Addis Ababa Events